አቶ በላይነህ ክንዴ ለለሚ እንጀራ ፋብሪካ ሶስት ተሽከርካሪዎችን አበረከቱ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ ለለሚ እንጀራ ፋብሪካ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎችን ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉን አቶ በላይነህ ክንዴ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስረክበዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት÷ ተሽከርካሪዎቹ የለሚ እንጀራ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ማምረት እንዲችል እያደረገ ባለው ጥረት በተቋሙ የሚሰሩ እናቶችን ለማመላለስ እንደሚውሉ ተናግረዋል፡፡
አቶ በላይነህ ክንዴም ለዚህ ዓላማ ላደረጉት የመለስተኛ ተሽከርካሪዎች ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡