Fana: At a Speed of Life!

ለእርዳታ ፈላጊዎች ፈጣን ድጋፍ ለማድረስ የተዋረድ መዋቅሩ ሙሉ አቅሙን መጠቀም ይኖርበታል- ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ አካባቢዎች ላሉ እርዳታ ፈላጊዎች ፈጣን ድጋፍ ለማድረስ የተዋረድ መዋቅሩ ሙሉ አቅሙን መጠቀም ይኖርበታል ሲል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) እንደገለጹት÷ለተጎጂዎች በፍጥነት እርዳታ ማድረስ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎች ቢኖሩም በኮሚሽኑ ቀጥታ ድጋፍ የሚደረገው ከወረዳ እስከ ክልል ካለው ተዋረድ አቅም በላይ ሲሆን ነው።

በመሆኑም ይህን ሂደት እስከሚያልፍ ድረስ የሚታዩ ክፍተቶች ሊኖሩ ይችላሉ ነው ያሉት።

መሰል ቅሬታዎችን ለማስቀረት የተዋረድ መዋቅሮች የቅድመ ዝግጅት አቅማቸውን ማጠናከር ይኖርባቸዋልም ብለዋል፡፡

በትዕግስት አብርሃም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.