Fana: At a Speed of Life!

አመራሩ የሚመዘነው የህዝቡን ጥያቄ ከመመለስ አንፃር ባስመዘገበው ውጤት ነው – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አመራሩ የሚመዘነው የህዝቡን ጥያቄ ከመመለስ አንፃር ባከናወነው ተግባርና ባስመዘገበው ውጤት መሆኑን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) ዛሬ ውይይት ያካሄደ ሲሆን፥ መድረኩ በዋናነት በክልሉ አዲስ ለተመደቡና ነባር አመራሮች የስራ መመሪያና ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

አቶ ኦርዲን በድሪ በመድረኩ በሰጡት የስራ መመሪያ፥ የአመራርነት ሚና ህዝቡን በቁርጠኝነት በማገልገል የየተቋማቱ ተልዕኮ በውጤታማነት እንዲሳካ በማድረግ በመልካምነት ሊታወስ የሚችል አሻራ ማሳረፍ ነው ብለዋል፡፡

በየተቋማቱ የሚታዩ ክፍተቶችን መሙላትና ጥንካሬዎችን ማጎልበት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው፥ ቅሬታዎችን ከመፍታት አንፃር ከመደበኛው አሰራር በመውጣትና አዳዲስ አሰራሮች በመዘርጋት ለህዝቡ ፍላጎት ፈጣን ምላሽ መስጠት ያስፈልጋልም ነው ያሉት፡፡

አመራሩ በሀላፊነት በቆየባቸው ጊዜያት የሚያከናውናቸው ተግባራት ከሀላፊነት ሲነሳ የማይፀፀትባቸው መሆን እንዳለባቸው መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ህዝቡን በፍትሃዊነት ማገልገል ከሁሉም አመራር እንደሚጠበቅ በመጥቀስም በአጭር ጊዜ የህዝብን እርካታ ሊያረጋግጡ የሚችሉ ተግባራት እውን ማድረግ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.