Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም ትብብራቸውን በይበልጥ ለማሳደግ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ረዳት ዋና ዳይሬክተር ቫለሪ ጓርኔሪ ጋር ዛሬ በጄኔቫ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል፡፡

በጄኔቫ እየተካሄደ ከሚገኘው 2ኛው ዓለም አቀፍ የሥደተኞች ፎረም ጎን ለጎን ባደረጉት ውይይት÷ ሁለቱም ወገኖች የተሻሻለውን የዕርዳታ ስርጭት ሥርዓት በመጠቀም በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎችን የበለጠ ለማፋጠን ተስማምተዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የዕርዳታ አቅርቦትን በድጋሚ በመጀመሩም አቶ ደመቀ አመስግነዋል፡፡

ድጋፉንም መንግሥት ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ብቻ እንዲደርስ ጥንቃቄ፣ ግልጽ፣ ውጤታማ እና ተጠያቂነት ያለው አሠራር መዘርጋቱን አረጋግጠዋል፡፡

ከምግብ እጥረት ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍም የዘላቂ ልማት መርሐ-ግብሮችን አስፈላጊነት ጠቁመው÷ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ እንዲሁም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እና ሌሎች የልማት መርሐ-ግብሮች በስኬት እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ቫለሪ ጓርኔሪ በበኩላቸው÷ ውጤታማ የዕርዳታ ስርጭት ሥርዓትን በማሻሻል ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት ላደረገው ትብብር እና ጠንካራ ቁርጠኝነት አመስግነዋል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራምም ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.