Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ባንክ ለዲጂታል መታወቂያ ትግበራ 350 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

የዓለም ባንክ ለዲጂታል መታወቂያ ትግበራ 350 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ለፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ትግበራ የሚውል የ350 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አድርጓል፡፡

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ዲጂታል መታወቂያ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አሰራር ለማዘመንና ዲጂታል ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡

ዲጂታል መታወቂያን በሀገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እና ሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የዓለም ባንክም ለፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ትግበራ የሚውል የ350 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አረጋግጠዋል፡፡

ድጋፉ በሀገር አቀፍ ደረጃ 90 ሚሊየን የሚሆኑ ዜጎች ዲጂታል መታዊቀያ እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

የተደረገው ድጋፍ በአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ እንደሚተገበር የጠቀሱት ዋና ስራ አስኪያጁ÷ይህም ለዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት ሚናው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ሁሉን አቀፍ፣ ወጥና አስተማማኝ የሀገሪቷ ነዋሪዎች የሚመዘገቡበት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚያስችልም አስረድተዋል፡፡

መታወቂያው በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ የግልፅነትና ተጠያቂነት አሰራር ስርዓት እንዲዘረጋና የተሳለጠ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት እንዲኖር አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አቶ ዮዳሄ የዓለም ባንክ የዲጂታል መታወቂያ ለኢትዮጵያ ያለውን ጠቀሜታ በመረዳት ላደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.