Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሀገራት አየር ኃይል አዛዦች የአየር ኃይል የውጊያ መሠረተ-ልማቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሀገራት አየር ኃይል አዛዦች እንዲሁም የሀገራት የአቪየሽን ተቋማት ኃላፊዎች የኢትዮጵያ አየር ኃይል ያስገነባቸው የውጊያ መሠረተ-ልማቶች እንዲሁም የትጥቅ አቅምን ለማሳደግ የተከናወኑ የለውጥ ስራዎችን ጎብኝተዋል።

“በመስዋዕትነት ሀገርን የዋጀ የኢትዮጵያ አየር ኃይል” በሚል መሪ ሀሳብ የኢትዮጵያ አየር ኃይል 88ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ከኅዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የአየር ምድቦችና ሁነቶች እየተከበረ ነው።

የመርሐ ግብሩ አካል የሆነ የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር ኃይል አዛዦች የምክክር መድረክ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት አየር ኃይል አዛዦች፣ የተለያዩ ሀገራት የአቪየሽን ተቋማት ኃላፊዎችና ወታደራዊ አታሼዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

የመድረኩ ዓላማ በኢትዮጵያ አየር ኃይል ከለውጡ ወዲህ የተሰሩትን ሥራዎችን ማስተዋወቅና የዘርፉን ሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር መሆኑ ተመልክቷል።

ከመድረኩ ጎን ለጎን አየር ኃይሉ ያስገነባቸው የውጊያ መሠረተ-ልማቶች እንዲሁም የትጥቅ አቅምን ለማሳደግ የተሰሩ ሥራዎች ምልከታ መካሄዱም ነው የተገለጸው።

በአየር ኃይሉ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በሰው ኃይል አቅም ግንባታ፣ የትጥቅ አቅምን በማዘመንና በመሠረተ-ልማት ግንባታ በኩል ሰፊ ሥራዎች መከናወናቸው በጉብኝቱ ተመልክቷል።

በተጨማሪም አየር ኃይሉ በግብርና ልማት እያከናወነ የሚገኘውን ዘርፈ ብዙ ተግባራት ላይ ምልከታ መደረጉን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.