Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዳያስፖራ አገልግሎት ያላትን ልምድ ለኬንያ አካፈለች

 

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ 60ኛ ዓመት የነፃነት ቀን አከባበር አካል የሆነው የዳያስፖራ ቀን በናይሮቢ በተከበረበት መድረክ ላይ ኢትዮጵያ በመስኩ ያላትን ተሞክሮ አካፍላለች።

በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እንድሪስ (ዶ/ር)÷ ኢትዮጵያ በዳያስፖራ ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥተው ከሚሰሩ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡

ዳያስፖራውን በእውቀትና ክህሎት ሽግግር እንዲሁም በኢንቨስትመንት ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

በአፍሪካዊ ወንድማማችነት እሳቤ ላይ በመመስረት በአህጉሪቱ በዳያስፖራ ላይ የሚሰሩ ተቋማት ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መስራት ይገባል ብለዋል።

የኬንያ የውጭ ጉዳይና የዳያስፖራ ሚኒስቴር የዳያስፖራ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሮዝሊን ንጆጉ በበኩላቸው÷ ኬንያ ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር የዳያስፖራን የልማት ተሳትፎ ለማጠናከር ትሰራለች ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በበዓሉ ላይ በዳያስፖራ ላይ የሚሰሩ የሀገራት ተወካዮች፣ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የሀገራት አምባሳደሮች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች እንዲሁም ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የመጡ የኬንያ ዳያስፖራ አባላት ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.