የሐረሪ ክልል ካቢኔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ምክር ቤቱ የሐረር የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ የልማት ድርጅትን ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በውይይ ላይ እንደገለፁት÷ መንግሥት ድሃ ተኮር በሆኑ የልማት ሥራዎች የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው፡፡
በተለይም ደንቡ በዝቅተኛ ኢኮኖሚ የሚተዳደረውን ኅብረተሰብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ የሕዝቡን የመግዛት ዐቅም ያገናዘበ የዳቦና የዱቄት ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ያስችላል ብለዋል።
የክልሉ ሕዝብና በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የማኀበረሰብ ክፍሎች የሚኖርባቸውን ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስ እንደሚያስችል መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
በዘርፉ የሥራ ዕድሎችን በማመቻቸት ዜጎች ራሳቸውን በገቢ እንዲያግዙ በማስቻል በክልሉ ለሚከናወኑ የማኀበራዊ ልማት ሥራዎች የራሱን ሚና እንደሚያበረክትም ነው ያብራሩት፡፡
የደንቡ ተግባራዊ መሆንም ጥራቱና ጤንነቱ የተረጋገጠ የሥርዓተ-ምግብ አቅርቦት እንዲኖረው የሚያስችል የዳቦና የስንዴ ምርትን ለማሟላት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስታውቀዋል፡፡
ፋብሪካው ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ በባለቤትነት እንዲያዝ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል፡፡
መስተዳድር ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ ተወያይቶ ከዛሬ ታኅሣስ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
የሐረር ዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካ በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት መገንባቱ ይታወሳል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!