Fana: At a Speed of Life!

“ጥቁር አንበሳ!” በሚል የተሠየመው የአየር ትርዒት በመካሄደ ላይ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት “ጥቁር አንበሳ!” በሚል የተሠየመው የአየር ትርዒት እየተካሄደ ይገኛል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ኅዳር 20 ቀን 1928 ዓ.ም የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ 88ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ለተከታታይ ቀናት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲያከብር የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለት የበዓሉ የማጠቃለያ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ እና የአረብ ኢሚሬት ፓይለቶች ተቀናጅተው የአየር ላይ ትርኢት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.