ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኩዌት ኤሚር ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኩዌት ኤሚር ናዋፍ አል-አሕመድ አል-ሳባህ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ መልዕክት፤ ለኩዌት ህዝብና መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል።
በ86 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ኤሚር ናዋፍ አል-አሕመድ አል-ሳባህ ከፈረንጆቹ 2006 ጀምሮ አልጋ ወራሽ ሆነው ተሰይመው ነበር፡፡
ከሦስት ዓመት በፊት በፈረንጆቹ 2020 በሥልጣን ላይ የነበሩትን የወንድማቸውን ሕልፈት ተከትሎ ነበር ወደመሪነት የመጡት።