Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል እየገነባ ያለው ዐቅም ትምህርት ሰጪ ነው – ወታደራዊ አታሼዎች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል እየገነባ ያለው ዐቅም ለአፍሪካ ሀገራት ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ወታደራዊ አታሼዎች ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ ብርጋዴር ጀነራል ጆክ አኖግ ዴንግ÷ የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል የአፍሪካ ሀገራት በወታደራዊ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ ትምህርት የሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከሌሎች ወታደራዊ አታሼዎች ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል እያከናወናቸው ያሉ ሥራዎችን በጎበኙበት ወቅትም በተመለከቷቸው ሥራዎች መደነቃቸውን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሴኔጋል ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ ሌተናል ኮሎኔል ማማዱ ፋል በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል ያለውን ሙያዊ ብቃትና ቁርጠኝነት መመልከታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በአጠቃላይ ዓየር ኃይሉ ያለበት ደረጃም እጅግ የላቀ መሆኑን ተመልክተናል ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት የጋራ የጦር ልምምድን ጨምሮ በወታደራዊ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዓየር ኃይልና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ዓየር ኃይል በጋራ “ጥቁር አንበሳ” የተሰኘ ልዩ የዓየር ላይ ትርዒት ትናናት በቢሾፍቱ ከተማ ባካሄዱበት ወቅት÷ በኢትዮጵያ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ወታደራዊ አታሼዎች መታደማቸው ይታወሳል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.