በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የበጋ ወራት የበጎ ፈቃድ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሔደ ነው
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ እና የበጋ ወራት የበጎ ፈቃድ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በዱራሜ ከተማ እየተካሔደ ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) እና ሌሎች በየደረጃው የሚገኙ የሥራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡