Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል 500 አባዎራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመስኖ ልማት ለአገልግሎት ክፍት ሊሆን ነው

 

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል 94 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት በማልማት 500 አባዎራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገለጸ፡፡

ፕሮጀክቱ የተገነባው የሐረሪ ክልል ግብርና ልማት ቢሮ ከኮሪያ መንግሥት ባገኘው 16 ሚሊየን ብር መሆኑም ተገልጿል፡፡

በድሬ ጠያራ ወረዳ በሱቁል ቀበሌ የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክቱ÷ 230 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ ዐቅም አለው መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በቅርቡም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እንደሚመረቅ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.