በጅቡቲ ፓርላማ አፈ-ጉባኤ የተመራ ልኡክ አዲስ አበባ ገባ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ ፓርላማ አፈ-ጉባኤ ዲሌታ መሀመድ የተመራ ልኡክ አዲስ አበባ ገብቷል።
ልኡኩ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አቀባበል አድርገውለታል።
አፈ ጉባኤው ዲሌታ መሀመድን ጨምሮ የኢትዮ-ጅቡቲ የወዳጅነት ቡድን ሊቀ መንበር እና ምክትል ሊቀመንበር እንዲሁም የጅቡቲ ፓርላማ አባላት በልዑኩ የተካተቱ መሆኑ ታውቋል።
ልኡኩ በሚኖረው ቆይታ የሁለቱን አገራት ፓርላማዎች ወዳጅነት በሚያጠናክሩ ስራዎች ዙሪያ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
እንዲሁም አፈ ጉባኤው ለፓርላማ አባላት ንግግር እንደሚያደርጉ እና የተለያዩ የልማት ስራዎችን እንደሚጎበኙም ይጠበቃል።