Fana: At a Speed of Life!

ከባሕር ዳር – ወልዲያ ያለውን ባለ 400 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከባሕር ዳር – ወልዲያ ያለውን ባለ 400 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት በተያዘው ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

በአጠቃላይ ከባሕር ዳር – ወልዲያ – ኮምቦልቻ ባለ 400 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክትን በሁለት የግንባታ ምዕራፍ ከፍሎ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የመጀመሪያው የግንባታ ምዕራፍ ከባሕርዳር እስከ ወልዲያ የሚደርሰውን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የሚያጠቃልል ሲሆን÷ ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ከወልዲያ እስከ ኮምቦልቻ ድረስ ያለውን እንደሚሸፍን ተገልጿል፡፡

የመጀመሪያውን የግንባታ ምዕራፍም በተያዘው በጀት ዓመት አጠናቅቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ነው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፕሮጀክቱ ሪዚደንት ሀብታሙ ተሾመ (ኢ/ር) ያስታወቁት፡፡

ከባሕርዳር እስከ ወልዲያ እንደሚተከሉ ከሚጠበቁት 640 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች መካከልም÷ 620 የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ተከላ ተጠናቅቋል ብለዋል፡፡

ቀሪ ምሰሶዎችን ለመትከል የሚያስችሉ ሥራዎችም እየተከናወኑ ነው ማለታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ አመላክቷል፡፡

ከባሕርዳር እስከ ወልዲያ የኮንዳክተር ገመድ ለመዘርጋት ከታሰበው 295 ነጥብ 87 ኪሎ ሜትር ውስጥ 222 ኪሎ ሜትር ማጠናቀቅ መቻሉንም ጠቅሰዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈፃፀምም 85 በመቶ መድረሱንም አረጋግጠዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የባሕር ዳር ከተማ፣ የደቡብ ጎንደር እና የሰሜን ወሎ ዞኖችን የሚያካልል በመሆኑ ከቁሳቁስ ሥርቆት እና ወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮች ግንባታውን እንዳያጓትቱት በየደረጃው ያሉ አመራሮች የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲያበረክቱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.