Fana: At a Speed of Life!

ግብጽ የጋራ ተጠቃሚነትና ፍትሃዊነትን ያልተከተለ አቋም ይዛለች – አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብጽ የጋራ ተጠቃሚነት እና ፍትሃዊነትን ያልተከተለ አቋም መያዟን የኢትዮጵያ ወገን ዋና ተደራዳሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)÷ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 4ኛ ዙር የሶስትዮሽ ድርድር ውጤትን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም÷ በአባይ ውሃ አጠቃቀምና በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተመለከተ ግብጽ ኢትዮጵያን በማይመለከት የቅኝ ግዛት ውል ላይ በማተኮሯ 4ኛው ዙር የሶስትዮሽ ድርድሩ ያለስምምነት ተጠናቋል ብለዋል።

በአዲስ አበባ የተካሔደው 4ኛው ዙር የሶስትዮሽ ድርድር ብዙ መሻሻሎች የተደረጉበትና የሀገራቱ ፍላጎቶች የተመዘገቡበት እንደነበርም አንስተዋል፡፡

አምባሳደር ስለሺ ድርቅንና የውሃ ድርሻን በተመለከተ ግብጽ የጋራ ተጠቃሚነትና ፍትሃዊነትን ያልተከተለ አቋም መያዟን ገልጸዋል።

በዚህም ድርድሩ ያለስምምነት መጠናቀቁን ነው ያስረዱት፡፡

ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ እና በፍትሐዊ ድርድር የሶስቱን ሀገራት ጥቅም የሚያስጠብቅ የመፍትሔ ሀሳብ ላይ ለመድረስ ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በመግለጫቸው፤ የህዳሴ ግድቡ ኮንክሪት ስራ በመጪው ሰኔ ወር እንደሚጠናቀቅ ጠቁመው፤ የግድቡ ግንባታ አሁን ላይ 94 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል።

በፍሬሕይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.