Fana: At a Speed of Life!

የ70 ዓመቱ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10 ልጆች አባትና የልጅ ልጆችን ያዩት አቶ ዮሐንስ አዲሴ በ70 ዓመታቸው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ለመማር ወደ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አቅንተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን ተቀብሏል፡፡

በአቀባበሉ ላይም የ70 ዓመቱ አዛውንት አቶ ዮሐንስ አዲሴ የበርካቶችን ቀልብ ስበዋል፡፡

አቶ ዮሐንስ በ2015 ዓ.ም የተሰጠውን ሀገር አቀፍ ፈተና አልፈው ወደ ተመደቡበት ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ ልዩ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

በልጅነታቸው ጎበዝ ተማሪ እንደነበሩና ባጋጠማቸው የአካል ጉዳት ምክንያት ለበርካታ ዓመታት ከትምህርት ገበታ ርቀው መቆታቸውንም በአቀባበሉ ላይ ተናግረዋል፡፡

ለትምህርት ካላቸው ፍላጎት አኳያም ያቋረጡትን ትምህርት በመቀጠል ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

በሀዲያ ዞን ዱና ወረዳ ለጠቦ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አዛውንቱ ተማሪ÷ ከተማሩበት ትምህርት ቤት የ2015 ዓ.ም በሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ካለፉ ጥቂት የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች አንዱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውንም በትጋት ለማስኬድ በቂ ዝግጅት አድርጌያለሁ ማለታቸውን የዩኒቨርሲቲው መረጃ አመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.