በኦሮሚያ ክልል 2 ነጥብ 27 ሚሊየን ሄክታር መሬት በስንዴ መሸፈኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል 2 ነጥብ 27 ሚሊየን ሄክታር መሬት በስንዴ መሸፈኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስታወቁ፡፡
አቶ ሽመልስ አብዲሳ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷የስንዴ ምርትና ምርታማነትን መጨመር የብልጽግና በር መክፈቻ ዋና ቁልፍ በማድረጋችን እየተሳካልን ነው ብለዋል።
በዚህም ዓመት በበጋ የመስኖ የስንዴ ልማት ከ 2 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱም ነው የተገለጸው፡፡
እስካሁን በክልሉ ከ2ነጥብ 575 ሚሊየን ሄክታር መሬት በላይ ማረስ መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡
ከታረሰው መሬትም 2 ነጥብ 27 ሚሊየን ሄክታር መሬት በስንዴ መሸፈኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አንስተዋል፡፡
በዚህ ዓመት ከ 105ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ከመስኖ ስንዴ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው የጠቆሙት፡፡