Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሉሜ ወረዳ በበጋ መስኖ የለማ የስንዴ ማሳ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ በበጋ መስኖ የለማ የስንዴ ማሳ ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት÷ ከአራት ዓመታት በፊት በክልሉ በ7 ሺህ ሔክታር መሬት ላይ በመስኖ የተጀመረው የስንዴ ልማት አሁን ላይ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታርን ተሻግሯል።

በምርት ዘመኑ 2 ነጥብ 6 ሚለየን ሄክታር መሬት ለማረስ ታቅዶ ከ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት ማረስ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

ከታረሰው መሬት ውስጥም 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ያህል ሔክታር መሬት በስንዴ ሰብል ተሸፍኗል ነው ያሉት አቶ ሽመልስ፡፡

ከዚህም ከ105 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል፡፡

በተጨማሪም ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ የዶሮ እርባታ ማዕከላት፣ የእንስሳት ማድለቢያዎች እና የእንስሳት ተዋጽኦ የሚሸጥባቸውን የንግድ ቦታዎች ጎብኝተዋል።

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.