Fana: At a Speed of Life!

በሸገር ከተማ ከ70 በላይ አዲስ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸገር ከተማ አስተዳደር ከ70 በላይ አዲስ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ መሆኑ ተገለጸ፡፡

እየተገነቡ ያሉት ትምህርት ቤቶች በአቅራቢያቸው ትምህርት ቤት ባለመኖሩ ምክንያት ትምህርታቸውን መከታተል ያልቻሉ  ተማሪዎችን ችግር ይፈታሉ ተብሏል፡፡

የሸገር ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፊራኪያ ካሣሁን እንደገለጹት÷በዘንድሮው አመት ከ70 በላይ አዲስ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ ይገኛሉ።

እየተገነቡ ከሚገኙት ውስጥ 20 ትምህርት ቤቶች ግንባታቸው መጠናቀቁን በመግለጽ ቀሪዎችም በዚሁ አመት እንደሚጠናቀቁ ጠቅሰዋል፡፡

በተለያዩ ድርጅቶችና ባለሃብቶች ትብብር  ጥገናና እድሳት የሚያስፈልጋቸው ትምህርት ቤቶችም እንዲታደሱ እየተደረገ ነው ብለዋል።

እንዲሁም በማሻሻያ ፕሮግራም 51 ትምህርት ቤቶችን ሞዴል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አቶ ፊራኪያ ካሣሁን ለፋና ብሮድካስታንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

የመማር ማስተማር ሂደቱ የተሳካና የተማሪዎች ውጤትን ሊያሻሽል በሚያስችል መልኩ ስራዎች እየተሰሩ  እንደሚገኝ  ኃላፊውው አመላክተዋል፡፡

በሸገር ከተማ አስተዳደር በአሁኑ ወቅት የትምህርት ትራንስፎርሜሽን ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.