በሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የተመራ ልኡክ ጅግጅጋ ገባ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የተመራ ልኡክ ዛሬ ጅግጅጋ ከተማ ገብቷል።
ልዑኩ ጅግጅጋ በሚገኘው ገራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊ ሲደርስም በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሐመድ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
የሶማሊላንድና የሶማሌ ክልል አመራሮችም በንግድ፣ በድንበር አከባቢ ባለው የፀጥታ ጉዳይ ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል ሲል የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት እውን የሚያደርግ፣ የባሕር በር አማራጮችን የሚያሰፋ፣ የሁለቱን ወገኖች የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲ፣ የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ሠነድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ መፈራረማቸው ይታወቃል።