ተጠባቂው 4ኛው ፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በታሪኩ በከፍተኛ የሽልማት መጠን ነገ ይጀምራል
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው 4ኛው ፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በታሪኩ በከፍተኛ የሽልማት መጠን ነገ በገና በዓል ዋዜማ በቀጥታ ሥርጭት እንደሚጀመር ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል፡፡
ውድድሩ÷ የፋና ላምሮት ምዕራፍ 13፣ ምዕራፍ 14 እና ምዕራፍ 15 አሸናፊዎችን እንደሚያገናኝም ነው የተገለጸው፡፡
በነገው ዕለትም የምድብ አንድ 8 ተወዳዳሪዎች ከዛየን ባንድ ጋር በሁለት ዙሮች ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
የዚህኛውን የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በአንደኛነት ለሚያጠናቅቅ ተወዳዳሪ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ሽልማት አዘጋጅቷል።
በአጠቃላይ ለሽልማት የሚውል 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ማዘጋጀቱንም ነው ተቋሙ ያስታወቀው፡፡
ነገ የሚጀመረውን የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድርም ተመልካቾች ከ6:00 ጀምሮ በፋና ቴሌቪዥን፣ በኤፍም ኤም 98 ነጥብ 1 እና በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች በቀጥታ ሥርጭት እንዲከታተሉ ተጋብዘዋል፡፡
ተመልካቾችም በ8222 የስልክ መስመር አጭር የጽሑፍ መልዕክት በመላክ በንቃት እንዲሳተፉ ተጠይቀዋል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተሰጥኦ ኖሯቸው ዕድሉን ያላገኙ ድምፃውያንን ወደመድረክ በማምጣት እንዲሁም ለሙዚቃው ዘርፍ ዕድገት የራሱን ዐሻራ ለማሳረፍ የሚጠበቅበትን ሚና እየተወጣ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በለምለም ዮሐንስ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!