አብርሆት ቤተመጻሕፍት ዓለም አቀፉን የሲልክ ሮድ የቤተመጻሕፍት ጥራት ጥምረት ተቀላቀለ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አብርሆት ቤተመጻሕፍት ዓለም አቀፉን የሲልክ ሮድ የቤተመጻሕፍት ጥራት ጥምረት መቀላቀሉ ተነገረ።
ቤተመጻሕፍቱ ይህንን ጥምረት የተቀላቀለው ከተገነባ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ጥራትና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት በመቻሉ መሆኑን መቀመጫውን ቻይና ያደረገው የሲልክ ሮድ ዓለም አቀፍ የቤተመጻሕፍት ጥምረት ይፋ አድርጓል።
ዓለም ላይ ከተገነቡት ቤተመጻሕፍት መካከል አብርሆት ቤተመጻሕፍት በአጭር ጊዜ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ የጥናት፣ የምርምር፣ የፈጠራ እንዲሁም የጥንታዊ መፅሃፍት መገኛ በመሆን ትኩረት መሳብ እንደቻለም ጥምረቱ ገልጿል፡፡
ተቋሙ የኢትዮጵያ ቤተ መጻሕፍት ብቻ ሳይሆን የደመቀ የእውቀት መዳረሻ ቦታ ነው ሲል የገለጸ ሲሆን ፥ ይህም 43ኛ ቤተመጻሕፍት ተቋማት ጥምረት ሆኖ መመዝገብ መቻሉን አስታውቋል።
አብርሆት ቤተ መጻሕፍት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነትና ድጋፍ ለምረቃ በቅቶ አንጸባራቂ አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደሚገኝ ነው ዓለም አቀፉ የቤተመጻሕፍት ጥምረት የገለጸው፡፡
በአሁኑ ጊዜ 300 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ የጥናትና ምርምር ውጤቶች፣120 ሺህ በላይ ዓለም አቀፍ የጥናትና ምርምር ውጤቶችን የያዘ ከመሆኑም ባሻገር በውስጡ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ መጽሃፍቶችን መያዙ ተጠቅሷል፡፡
የአብርሆት ቤተመጻሕፍት አስገራሚ ግንባታና አቀማመጥ እንደዚሁም ዙሪያ ግቢው የተላበሰው አረንጓዴያማ ገፅታ የተቋሙን ሞገስ ከፍ ከማድረጉም በላይ የዜጎች የንባብ ፍላጎት እንዲነሳሳ እንደሚጋብዝም ተመላክቷል፡
አብርሆት ቤተመጻሕፍት በቀን ከ10 ሺህ በላይ አንባቢዎችን እያስተናገደ የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ ግዙፍ ተቋም ነው።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!