ተሳፋሪን አጉላልተዋል የተባሉ 823 አሽከርካሪዎች ተቀጡ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ተሳፋሪን አጉላልተዋል የተባሉ 823 የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች ከ596 ሺህ ብር በላይ ተቀጡ፡፡
የገንዘብ ቅጣት ከተላለፈባቸው በተጨማሪ በምክር የታለፉ መኖራቸውን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዳዊት ዘለቀ (ኢ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
ቢሮው ተሳፋሪን በሚያጉላሉ አሽከርካሪዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ያስታወቁት፡፡
በተጨማሪም ከ1 ሺህ 418 በላይ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሥራ የተሰማሩ አሽከርካሪዎች ከታሪፍ በላይ ሲያስከፍሉ በመገኘታቸው በገንዘብ እንዲቀጡ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡
በታሪክ አዱኛ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!