47ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ስብሰባ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 47ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ስብስባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማህማትና የሕብረቱ አመራሮች፣ የኮሚቴው ሰብሳቢ እና የሕብረቱ አባል ሀገራት አምባሳደሮች እየተሳተፉ ነው።
ስብስባው የካቲት 5 እና 6 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው 44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ እንዲሁም የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚከናወነው 37ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።
እንዲሁም ኮሚቴው በሕብረቱ ስር የሚገኙ ተቋማት አፈጻጸም እና በፈረንጆቹ 2023 ያካሄዷቸውን ስብስባዎች የተመለከቱ ሪፖርቶችን እንደሚያደምጥ ከአፍሪካ ሕብረት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
የሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ስብሰባ እስከ ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚቆይም ተገልጿል፡፡