በንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ ላይ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ ላይ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እንዳስታወቀው÷ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ በንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ ላይ የተከሰተውን የእሳት አደጋ በተደረገ ርብርብ ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር ተችሏል።
የአደጋው መንስኤ እና ሌሎች መረጃዎች እየተጣሩ መሆኑንም ኮሚሽኑ አመላክቷል፡፡