Fana: At a Speed of Life!

ክልሉ ከ3 ሺህ 500 ቶን በላይ የሻይ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከ3 ሺህ 500 ቶን በላይ የሻይ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን የክልሉ ቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን አስታወቀ።

በሻይ ምርታማነቱ የሚታወቀው ክልሉ በበጀት ዓመቱ ከ7 ሺህ ቶን በላይ የሻይ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ ተናግረዋል፡፡

በመጀመሪያው የበጀት ዓመቱ አጋማሽ ከ3 ሺህ 500 ቶን በላይ የሻይ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ ተችሏልም ብለዋል፡፡

የሻይ ምርትን የማስፋት እና ጥራትን የማስጠበቅ ስራ በክልሉ ቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን በኩል በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ÷ ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

የሻይ ምርትን ለማስፋት የሻይ ችግኝ የማፍላት ስራም በትኩረት ከወዲሁ እየተሰራ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡

በተመስገን ይመር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.