አቶ አረጋ ከበደ ከጣና ፎረም አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ከጣና ፎረም አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በቀጣይ ለሚካሄደው 11ኛው የጣና ፎረም ጉባዔ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ዙሪያ መክረዋል፡፡
11ኛው የጣና ከፍተኛ የአፍሪካ ሠላምና ደኅንነት ፎረም በተለያዩ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ጣና ፎረም ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በአፍሪካ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መፍትሔ ለማፈላለግ የተቋቋመና በኢኮኖሚ፣ ሰላም፣ ንግድ ትስስር እና የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም ዙሪያ የሚመክር ተቋም ነው፡፡