Fana: At a Speed of Life!

ለ40 ሺህ አረጋውያን የዓይን ሕክምና እንደሚሰጥ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ለ40 ሺህ አረጋውያን ነፃ የዓይን ሕክምና እንደሚሰጥ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ እና አልባሳር ዓለም አቀፍ ፋውንዴሽን በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ÷ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ለአረጋውያን ዜጎች በተመላላሽ ህክምና፣ በዓይን ቀዶ ህክምና፣ በሌንስ እና በመነጽር አገልግሎት የዓይን ህክምና በየዓመቱ ሲሰጥ ቆይቷል ብለዋል፡፡

ዘንድሮም በሶማሌ፣ በአፋር፣ በትግራይ እና ሌሎች አካባቢዎች በዓይን ሞራ ቀዶ ሕክምና የመነፅር ድጋፍ እና ሌሎች አገልግሎቶች ይሰጣሉ ነው ያሉት፡፡

አልባሳር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን የዓይን ሕክምና ማዕከል በያሲን ፋውንዴሽን አስተባባሪነት ከሚኒስቴሩ ጋር የአረጋውያንን የጤና ችግር ለመፍታት በኢትዮጵያ የዓይን ምርመራና ሕክምና አገልግሎትን በመስጠት አረጋውያንን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደተቻለም መገለጹን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ጥናት በማድረግ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጥቦቸውን ቦታዎች እንደሚመርጥ የተገለጸ ሲሆን÷ ሙሉ በሙሉ የሕክምና አገልግሎቱ በነጻ የሚሰጠው በአልባሳር ዓለም አቀፍ ፋውንዴሽን መሆኑ ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.