የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ፒያሳ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለጎብኚዎች ክፍት መሆኑ ተገለጸ፡፡
ክፍት መሆኑን ተከትሎም በአዲስ አበባ ከተማ ሥር ያሉ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸው ወቅትም የዓድዋ ድል የኢትዮጵያና የአፍሪካ ሕዝቦች የጀግንነት ተምሳሌት እና የነፃነት አርማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ታሪካችንን ከመስማት በዘለለ የዓድዋ ድል መታሰቢያ በእውን እንድናይና እንድንረዳ አስችሎናል ማለታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡