Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኩል ጥሪ አቀረበች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ጥያቄ ያቀረቡት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው 44ኛው የአፍሪካ ኅብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያ ያቀረበችው ጥያቄ ከአፍሪካ የ2063 አጀንዳ ጋር የሚጣጠም መሆኑን አንስተዋል።

ያም ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን ሀገር በቀል ቋንቋዎች ለማጠናከር የተያዘውን የአፍሪካ ኅብረት ግብ ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑንም ነው በማብራሪያቸው ያነሱት።

የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቻርተር የተፈረመው አማርኛን ጨምሮ በአራት ቋንቋዎች መሆናቸውን እንዳስታወሱም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አምባሳደር ታዬ አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ ማድረግ የአፍሪካ የቋንቋ ብዝኃነት መቀበልና የጋራ ማንነትን ማጠናከር ነው ብለዋል።

ይህም አህጉሪቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እገዛ እንደሚያደርግ ነው የጠቆሙት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.