ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከዩኤንዲፒ ረዳት ዋና ፀሃፊና የአፍሪካ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴከተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) ረዳት ዋና ፀሃፊ እና የአፍሪካ ዳይሬክተር አሁና ኤዚያኮንዋ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የተለያዩ የልማት ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተገልጿል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ÷ዩኤንዲፒ በኢትዮጵ ላከናወናቸውና እየሠራቸው ላሉ ተግባራት ማመስገናቸውን የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
በሌላ በኩል ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ሴቶችን በግብርና ማብቃት ላይ ባተኮረ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር÷“በገጠር የሚገኙ ሴቶችን ማብቃት የፍትሕ፣ የእኩልነትና የሰብዓዊ መብት ጥያቄ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ሴቶችን በግብርና ዘርፍ ለማብቃት ጥረት ማደረግ እንደሚገባ ጠቁመው÷በዚህም ለሁሉም ሴቶች የመልማት ተስፋ ያለበትና አፍሪካ ለመጪው ትውልድ የመልካም ዕድል ብርሃን የምትፈነጥቅበት ጊዜ መገንባት እንችላለን ብለዋል፡፡