ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የተለያየ ሹመት ሰጡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሹመት ሰጥተዋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1. አቶ አስር ኢብራሂም – የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
2. አቶ አልጀሊ ሙሳ – የክልሉ ሚዲያ ዋና ዳይሬክተር፣
3. አቶ ብርሀኑ አየሁ – የርዕሰ መስተዳድር የሕግ አማካሪ፣
4. አቶ በቀለ አንበሳ – የርዕሰ መሰተዳድር የኢኮኖሚ አማካሪ፣
5. አቶ አስማማው አብሾክ – የክልሉ ፍትህ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ፣
6. አቶ አብዱልከሪም ሙሳ – በክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ፣
7. አቶ ሉቁማን አብዱልቃድር – የአካባቢ ደን ሀብት ጥበቃ አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን፣
8. አቶ ሁሴን ሀሰን – በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ
9. አቶ አህመድ ሙሳ – በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን ም/ዋና አስተዳዳሪ ሆነው መሾማቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡