Fana: At a Speed of Life!

የታክስ አስተዳደርን ማሻሻልና የክልሎችን ገቢ አሰባሰብ አቅም ማሳደግ የቀጣይ ትኩረት ይሆናል – ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የታክስ አስተዳደርን ማሻሻልና የክልሎችን ገቢ አሰባሰብ አቅም ማሳደግ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ እንደሚሆን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ አመለከቱ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የበጀት ዓመቱ ሁለተኛው ሩብ የስራ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው።

በግምገማው መድረኩ የገቢ ዘርፉ አፈጻጸም እንደታየ የገለጹት ሚኒስትሯ፤ በበጀት ዓመቱ 529 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን አስታውሰዋል።

ዕቅዱን ለማሳካት በተሰራው ስራ በመጀመሪያ ስድስት ወራት 302 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።

አንዳንድ ቅርንጫፎች ባሉበት አካባቢ ችግር ቢኖርም ገቢ አሰባሰቡ በፈተናዎች ውስጥ እያለፈም የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገብ እንደቻለ አስረድተዋል።

ከሀገራዊ የኢኮኖሚ አቅም አንጻር እየተሰበሰበ ያለው ገቢ ዝቅተኛ መሆኑን ገልጸው፤ ይህንን ለመቀየር የታክስ አስተዳደርን ማሻሻልና የክልሎችን ገቢ አሰባሰብ አቅም ማሳደግ ላይ በቀጣይ ትኩረት እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በኮንትሮባንድ መስፋፋት፣ ህገወጥ ንግድ፣ በስነ-ምግባር ጉድለትና በሌብነት የገቢ አሰባሰቡን እየተፈተነ በመሆኑ ችግሮቹን በዘላቂነት ለመፍታት የጋራ ትግል እንደሚጠይቅ ገልጸዋል።

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.