የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመረቁ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አምቦ፣ ወላይታ ሶዶ እና ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል፡፡
አምቦ ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስ እና በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 714 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
በተመሳሳይ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 804 ተማሪዎችን አስመርቋል።
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲም በ2ኛ ዲግሪና በመጀመሪያ ዲግሪ ያስተማራቸውን 361 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን÷ ፥ ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው 361 ተመራቂዎች መካከል 39ኙ በ2ኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።
ቀሪዎቹ 322 ተማሪዎች ደግሞ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆኑ ፥ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎቹ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ በፋርማሲና በነርሲንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን በመደበኛ እንዲሁም በቅዳሜና እሑድ መርሐ ግብር ሲከታተሉ የነበሩ ናቸው።
በመለሰ ታደለ እና ዓለማየሁ መቃሳ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!