Fana: At a Speed of Life!

ለዚህ ስኬት አብራችሁን ለሰራችሁ እና ለደገፋችሁን ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዚህ ስኬት አብራችሁን ለሰራችሁ እና ለደገፋችሁን ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ሲሉ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ መሪ ሽልማትን ያሸነፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገዉ እና በየዓመቱ በአፍሪካ ምርጥ ብቃት ያሳዩ አፍሪካውያን መሪዎችን የሚሸልመው የአፍሪካ ሊደርሺፕ መጽሄት የሚያዘጋጀው የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ መሪ ሽልማትን አሸንፈዋል።

ሽልማቱን ያሸነፉት የመጀመሪያ የአዲስ አበባ ሴት ከንቲባ መሆናቸው ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሙስናን በመዋጋት፣ ተቋማዊ ሪፎርሞችን በመተግበር፣ መልካም አስተዳደር በማስፈን፣ በአመራር ብስለት እንዲሁም ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች ላይ ባሳዩት ውጤታማ ስራ መሆኑም ተገልጿል።

ከቀድሞ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጃካያ ኪኪዌቴ እጅ ሽልማቱን የተቀበሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ሽልማትን አሸናፊ በመሆኔ ክብር እና ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል።

ሽልማቱ የጋራ ትጋት ዉጤት መሆኑን ገልጸው፤ ለዚህ ስኬት አብራችሁን ለሰራችሁ እና ለደገፋችሁን ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ሲሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.