Fana: At a Speed of Life!

ለሽብር ተግባር ሊውሉ የነበሩ የጦር ሜዳ መገናኛ ሬዲዮዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ለሽብር ተግባር ሊውሉ የነበሩ የጦር ሜዳ መገናኛ ሬዲዮዎች መያዛቸውን የጌዲኦ ዞን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ሕገ-ወጥ መገናኛ ሬዲዮዎቹ መነሻቸው ሞያሌ ያደረጉ እንደነበር የጌዴኦ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ግርማ በየነ ተናግረዋል፡፡

ከሕገ ወጥ ድርጊቱ ጋር በተያያዘም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ፖሊስ ከሕብረተሰቡ ጋር በቅንጅት መስራቱ ሕገ ወጥ የመገናኛ መሣሪያዎቹን የመያዝ ሥራውን ውጤታማ እንዳደረገው መጥቀሳቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.