በኦሮሚያ ክልል የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ የፊታችን ቅዳሜ በይፋ ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ የፊታችን ቅዳሜ በይፋ የሚጀመር መሆኑን የክልሉ ሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት ቢሮ አስታውቋል።
በበጎ ፈቃድ ሥራው 7 ሚሊዮን ወጣቶች የሚሳተፉ መሆኑም ነው የተገለጸው ።
የኦሮሚያ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ሁሴን ዝናቡ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ የበጎ ፈቃድ ሥራው የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 6 ቀን 2012 ዓ.ም በይፋ ይጀመራል።
ለዚሁ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትም 7 ሚሊዮን ወጣቶች ተሳታፊ ሲሆኑ÷በጎ ፈቃደኛ ወጣቶቹም በደም ልገሳ፣ ኮሮናን በመከላከል፣ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም ችግኞችን ይተክላሉ።
ለሶስት ወራት በሚቆየው የበጎ ፈቃደኝነት ሥራ 10 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ መታሰቡንም አቶ ሁሴን ገልጸዋል።
ወጣቶቹ ከክልሉ ባሻገር በሌሎች አካባቢዎችም የበጎ አድራጎት ሥራ ለማከናወን መዘጋጀታቸውን አቶ ሁሴን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።