Fana: At a Speed of Life!

ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ ተጀመረ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ በአዲስ አባባ መካሄድ ጀምሯል።

በጉባዔው የሃይማኖት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ አምባሳደሮች፣ የአፍሪካና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

በአህጉርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ሠላምና ልማትን ማረጋገጥ፣ ሰብዓዊ ክብርን መጠበቅ፣ አካባቢን መጠበቅ፣ የጥላቻ ንግግርንና መጤ ጠልነትን በጋራ መከላከል የሚያስችል ምክክር ማድረግ የጉባኤው ዋና ዓላማ መሆኑ ተገልጿል።

ጉባዔው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የበላይ ጠባቂነት የተዘጋጀ ሲሆን ዛሬ እና ነገ እንደሚካሄድ ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.