Fana: At a Speed of Life!

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 ፣(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ከሆኑት ጆሃን ቦርግስታም ጋር ተወያዩ።

አቶ ገዱ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ባላት ስትራቴጂያዊ እና ሁሉን አቀፍ ትብብር ደስተኛ መሆኗን ገልጸው÷ ይህንኑ በተሻለ አጠናክራ ለማስቀጠል በትኩረት ትሰራለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጤና ስጋት የሆነውን የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል በምታደረገው ጥረት የአውሮፓ ህብረት እያደረገ ስላለው ድጋፍም  ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አቶ ገዱ አያይዘውም ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ከዚህ ቀደም የጀመሩትን ውይይት ለማስቀጠል በሚያደርጉት ውይይት የአውሮፓ ህብረት በታዛቢነት በመሳተፉ ኢትዮጵያ ደስተኛ መሆኗን ጠቁመዋል።

ግድቡ የደረሰበትን ደረጃ እና እስከዘሬ ድረስ በሶስቱ አገሮች የተደረጉ ውይይቶቸን በተመለከተም  አቶ ገዱ ለአምባሳደሩ ገለጻ አድርገዋል።

አምባሳደር ጆሃን ቦርግስታም በበኩላቸው ÷የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እያደረገች ያለውን ጥረት በማድነቅ የአውሮፓ ህብረት በዚህ በኩል የሚያደርገውን ድጋፍም አጠናከሮ ይቀጥላል ብለዋል።

አምባሳደሩ አያይዘውም ሶስቱ አገሮች ከግደቡ ጋር በተያያዘ ያላቸውን ልዩነት በውይይት እንዲፈቱ የአውሮፓ ህብረት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ መግለጻቸውንከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.