ኦቪድ ኮንስትራክሽን ግርፕ ለ ጽዱ ኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶን የ 16 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦቪድ ኮንስትራክሽን በስሩ ባሉት ድርጅቶች ስም 15 ሚሊየን ብር እንዲሁም የኦቪድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዮናስ ታደሰ በግላቸው የ 1 ሚሊየን ብር፤ በድምሩ 16 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
የጽዱ ኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶን እንደቀጠለ ሲሆን÷ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ዜጎች እንዲሁም ተቋማት በንቅናቄው እያደረጉት ያለው ተሳትፎ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡