አምባሳደር ምስጋኑ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አወር ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች እንዲሁም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
አምባሳደር ምስጋኑ÷በኢትዮጵያና ጀርመን መካከል ያለው ዘርፈ ብዙ ግንኙት እንዲጎለበት አምባሳደር ስቴፈን አወር ላበረከቱት አስተዋጽኦ ማመስገናቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል፡፡