አምባሳደር ታዬ ከካናዳ ዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከካናዳ ዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር አሕመድ ሁሴን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ÷አምባሳደር ታዬ ኢትዮጵያ ከካናዳ ጋር ላላት ጠንካራ ግንኙነት ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ አውስተዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም በኢትዮጵያ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸው ተገልጿል፡፡