Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ በሰው ተኮር ስራዎቿ ማኅበራዊ ፍትህን ለማንገስ ያለ እረፍት በመስራት የስበት ማዕከል እየሆነች ነው- ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ በሰው ተኮር ስራዎቿ ማኅበራዊ ፍትህን ለማንገስ ያለ እረፍት በመስራት የስበት ማዕከል እየሆነች ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩ ጽሑፍ÷ባለፉት ቀናት ለአፍሪካ መሪዎች የትውልድ ግንባታ ሥራ የሆነው የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ላይ ያለንን ልምድ አጋርተናል ብለዋል።

የአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በታላላቅ ፕሮጀክቶቿ አጊጣ፤ በሰው ተኮር ስራዎቿ ማኅበራዊ ፍትህን ለማንገስ ያለ እረፍት በመስራት የስበት ማዕከል እየሆነች ነው ሲሉም ገልጸዋል።

መርሐ ግብሩ እንዲሳካ በአጋርነት ሲሰራ ለነበረው ቢግ ዊን ፊላንትሮፒን እና ሲያስተባብሩ ለነበሩ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.