ሰርጂም ራትክሊፍ ከ6 ቢሊየን ፓውንድ በላይ ከሰሩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማንቼስተር ዩናይትድ አነስተኛ ድርሻ ባለቤት ሰር ጂም ራትክሊፍ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ6 ቢሊየን ፓውንድ በላይ ከስረዋል፡፡
እንግሊዛዊው ባለሀብት ሰር ጂም ራትክሊፍ ሀብታቸው ከ23 ነጥብ 519 ቢሊየን ፓውንድ ወደ 17 ነጥብ 046 ቢሊየን ፓውንድ ገደማ ዝቅ ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል።
የ72 ዓመቱ ባለሃብት ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ከአጠቃላይ ሀብታቸው አንድ አራተኛ ሀብታቸውን ማጣታቸውን ዘገባው አመላክቷል፡፡
በዚህም በእንግሊዝ ከ350 ሀብታም ሰዎች ዓመታዊ ዝርዝር ውስጥ ከአራተኛ ወደ ሰባተኛ ዝቅ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
የራትክሊፍ ኢኒኦስ ግሩፕ በፈረንጆቹ የካቲት 2024 የማንቼስተር ዩናይትድን አንድ አራተኛ አክሲዮን ገዝቶ እግር ኳሳዊ ጉዳዮችን እያሥተዳደረ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
ባለሃብቱ በኦልድትራፎርድ የማንቼስተር ዩናይትድን የትኬት ዋጋ ከፍ በማድረግ እና የክለቡን ፋይናንስ ለማሻሻል በርካታ የክለቡን ሠራተኞች በሁለት ዙር መቀነሳቸው ይታወሳል፡፡
የራትክሊፍ አሥተዳደር ለወጪ ቅነሳ በሚል ምክንያት የክለቡን ሠራተኞች መቀነስ በርካታ የክለቡን ደጋፊዎች ማስቆጣቱ አይዘነጋም፡፡
ማንቼስተር ዩናይትድ በፕሪሚየር ሊጉ ሁለት ጨዋታዎች እየቀሩት በ39 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የክለቡ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተስፋ እና የሽልማት ገንዘብ በቀጣይ ሳምንት ከቶተንሃም ሆትስፐር ጋር በሚያደርገው የዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ይወሰናል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ