Fana: At a Speed of Life!

አልጄሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደምታጠናክር ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አልጄሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሕዝብ ለሕዝብና ፓርላሜንታዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማሳደግ እንደምትፈልግ ገለጸች።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጪ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሀገራቱ መካከል በሚመሰረተው የፓርላሜንታዊ ዲፕሎማሲ ቡድንና አጠቃላይ ግንኙነት ዙሪያ በኢትዮጵያ የአልጄሪያ አምባሳደር ሞሐመድ ላምኔ አባስ ጋር ተወያይቷል።

ሀገራቱ ያላቸውን ጠንካራ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማሳደግና በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች በጋራ ለመስራት አልጀሪያ ፍላጎት እንዳላት አምባሳደር ሞሐመድ ገልጸዋል።

ፓርላሜንታዊ ዲፕሎማሲ በሀገራት መካከል ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶችን ከማሳደግ ባለፈ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይት የመፍታት አቅም እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ እየተመዘገቡ ባሉ ዘርፈ ብዙ ስኬቶች የአልጄሪያ መንግስት ደስተኛ መሆኑን አምባሳደሩ መግለጻቸውንም የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.