የ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰዎች ንጽህናውን በጠበቀ ቦታ በመጸዳዳት አካባቢን ንጹህ የማድረግ ባህልን እንዲያሳድጉ ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃዎች እንዲሠሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ በሆነው የ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ የሚያደርጉት ተሳትፎ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።
ተሾመ ጉዴ ደሜ 200 ሺህ ብር እንዲሁም ዙቤዳ ከድር አህመድ 100 ሺህ ብር በማበርከት ብቅናቄውን ተቀላቅለዋል።
ለ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ዜጎች ተሳትፎ ማድረጋቸውን የቀጠሉ ሲሆን÷ ግንቦት 4 ቀን 2016 በተካሄደ ዲጂታል ቴሌቶን በአንድ ጀምበር ከ154 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ይታወሳል፡፡
ለ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው የሂሳብ ቁጥር 1000623230248፣ በብሔራዊ ባንክ የዶላር አካውንት 0101211300016 እና በስዊፍት ኮድ NBETETAA ድጋፍ በማድረግ የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄን ይቀላቀሉ፡፡