Fana: At a Speed of Life!

የሶማሊ ክልል የጎሳ መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት መሪዎች የህዳሴ ግድብን እውን ለማድረግ ከመንግስት ጎን እንደሚቆሙ አረጋገጡ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊ ክልል የሚገኙ የተለያዩ የጎሳ መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት መሪዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከተወያዩ በኋላ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

የጎሳ መሪዎቹ፣ የሀገር ሽማግሌዎቹ እና የሀይማኖት መሪዎቹ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ እና የክልሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

በዚህም የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታን በተመለከተ ኢትዮጵያ ወንዞቿን የመጠቀም መብቷ መጠበቅ ስላለበት የግድቡን ፍፃሜ እውን ለማድረግ ከመንግስት ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት አሁን ባለው የኮሮና በሽታ ወረርሽኝ ምክንያት በዚህ ዓመት ሊካሄድ የነበረውን 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ማራዘሙን አስታውሰው አሁን ያለዉን ተጨባጭ ሁኔታ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የፌደሬሽን ምክር ቤት ምርጫው እንዲራዘም መወሰኑ ተገቢነት ያለው መሆኑን አንስተዋል።

መንግስት በሚያደርጋቸው ሀገር የሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ የክልሉ ህዝብና መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርጉም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.