Fana: At a Speed of Life!

ታንዛኒያ በሰላምና ደኅንነት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር እንደምታጠናክር ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ታንዛኒያ በሰላምና ደኅንነት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር እንደምታጠናክር የሀገሪቱ የመከላከያና ብሔራዊ አገልግሎት ሚኒስትር ስቴርጎሜና ላውረንስ ገለጹ።

ሚኒስትሯ ÷ታንዛኒያና ኢትዮጵያ በሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ያላቸው ታሪካዊ ትብብር አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።

ሁለቱ ሀገራት በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ በትብብር ለመሥራት የተፈራረሙትን የመግባቢያ ሥምምነት ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑንም አስታውሰዋል።

ታንዛኒያ በቀጣናው እንዲሁም በአህጉር ደረጃ የሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር እንደምታጠናክር ገልፀዋል።

በሰው ሃይል ልማት ትብብር ኢትዮጵያ የታንዛኒያን ሙያተኞች በማሰልጠን ትልቅ አስተዋጽዖ እያደረገች መሆኑንም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ትልቅ ሚና እየተጫወተች መሆኗን ሚኒስትሯ ለኢዜአ ገልፀዋል።

የሁለቱን ሀገራት የሰላምና ጸጥታ ትብብር መስክ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ታንዛኒያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ ከመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ጋር በዚህ ሳምንት መወያየታቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.