1 ሺህ 181 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 181 ኢትዮጵያውያን ዛሬ በተካሄዱ ሦስት ዙር በረራዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ከሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራም 41ሺህ 700 ኢትዮጵያውያን መመለሳቸውን ነው ያስታወቀው፡፡